የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ካርዲናል በአውስትራልያ ተቃውሞ ገጠማቸው
-
- Posts: 396
- Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ካርዲናል በአውስትራልያ ተቃውሞ ገጠማቸው
በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን የጄኖሳይድ ወንጀል አሁንም እየቀጠለ ባለበት ወቅት በመላው አለም የሚገኙ የትግራይ ልጆች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይህንን የጄኖሳይድ ወንጀል እንዲፈፀም የተባበሩ አካላት እያጋለጠ መጥቷል። ለበርካታ የፋሽስቱ አብይ አህመድ ባለስልጣናት የሀፍረት ካባ በማከናነብ የተጀመረው ተግባር ጦርነቱን ባርከው ባስጀመሩ የሃይማኖት አባቶች ላይም ቀጥሏል።
በአውስትራልያ አንዲት ትግራወይቲ ወጣት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ካርዲናል ብርሃነየሱስ ባገኘችው አጋጣሚ ለምን የትግራይ ህዝብ ሲጨፈጨፍ አላወገዙም፣ እንደሃይማኖት አባትነትዎ ግዴታዎን አልተወጡም። የትግራይ ከበባ እያዩ ለምን ዝም አሉ ሰትል በጨዋ ፣በሰከነ አንደበት ስትጠይቃቸው የሚያሳይ የቪድዩ ምስል በስፋት እየተሰራጨ ሲሆን ወጣቷ ካርዲናሉ በትግራይ ህዝብ ለተከፈተው ወረራ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሰራዊትን ባርከው ሲልኩ የሚያሳይ የቪድዮና የፎቶ ማስረጃ አለኝ ስትልም ተደምጣለች።