Meles Zenawi

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 396
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

Meles Zenawi

Post by africangear »

1. ግንቦት 1 ቀን 1947 ዓ.ም ከእናታቸው ከወይዘሮ አለማሽ ገብረልዑልና ከአባታቸው ከአቶ ዜናዊ አስረስ በአድዋ ከተማ ተወለዱ።
ትምህርት
2. እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በዓድዋ ንግሥተ ሳባ ትምህርት ቤት ተማሩ፡፡ ከ1961 እስከ 1964 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት አዲስ አበባ ተከታተሉ።
3. በ1965 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ የሕክምና ትምህርታቸውን መከታተል ጀመሩ።
የፖለቲካ ተሳትፎ
4. በ1966 መጀመሪያ በተማሪዎች መማክርት ምርጫ ላይ በመወዳደር የሣይንስ ፋኩልቲን በመወከል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምክር ቤት (Student Council) አባል በመሆን የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ አመራርን ተቀላቀሉ።
5. በመስከረም ወር 1967 ዓ.ም የብሔረ ትግራይ ተራማጆች ማህበር (ማገብት) እንደተመሠረተ የንቅናቄው አባል ሆኑ።
6. በ1967 ዓ.ም አምባገነኑን የደርግ ሥርዓት ለመታገል ወደ ትጥቅ ትግል በመውጣት የተሃህት/ህወሓት አባል ሆኑ፡፡ ከ1967 እስከ 1969 በህወሓት ታሪክ የድርጅት ህልውናን የማረጋገጥ ምዕራፍ ፈተናዎች በፅናት ተሻገሩ።
7. በ1969 ዓ.ም የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ተወካይና የከፍተኛ አመራር አባል ሆኑ።
8. በ1971 ዓ.ም በህወሓት 1ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ፡፡
9. ከ1971-1975 ዓ.ም የትግራይን ሕዝብ በብሔራዊና ህዝባዊ ትግሉ በስፋት ለማሳተፍ በተደረገው እንቅስቃሴ በአመራርነት ተሳተፉ።
10. በ1975 ዓ.ም በሁለተኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴና የፖሊት ቢሮ አባል ሆነው ተመረጡ።
11. ከ1976-1981 ዓ.ም የህወሓት የትግል እንቅስቃሴን ከኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል ጋር ለማስተሳሰር ከፍተኛ የጥናትና የአመራር ሚና ተጫወቱ።
12. በ1981 ዓ.ም በሦስተኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ የህወሓት ዋና ጸሐፊ በመሆን ተመረጡ።
13. በ1983 ዓ.ም ህዳር ወር በኢህአዴግ የመጀመሪያ ጉባኤ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።
መንግሥታዊ የአመራር ተሳትፎ
14. በ1983 ዓ.ም ግንቦት ወር ኢህአዴግ አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት የኢህአዴግ ጊዜያዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሆነው ለአንድ ወር ያህል አገለገሉ።
15. ከሐምሌ ወር 1983 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1987 ዓ.ም መጨረሻ የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ፕሬዚዳንት በመሆን አገለገሉ።
16. በ1987ዓ.ም የተካሄደውን የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ተከትሎ በመስከረም 1988 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ተመረጡ።
17. በ1992 ዓ.ም ሁለተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በመስከረም 1993ዓ.ም ተመረጡ።
18. በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ሦስተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በ1998ዓ.ም መስከረም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ለ3ኛ ጊዜ ተመረጡ።
19. በ2002 ዓ.ም የተካሄደውን አራተኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ በ2003 ዓ.ም መስከረም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ለአራተኛ ጊዜ በመመረጥ እስከ ዕለተ ህልፈታቸው አገራቸውንና ሕዝባቸውን አገልግለዋል፡፡
20. ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘና በሌሎች ጉዳዮች የአፍሪካን ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ፣በቡድን 8 እና ቡድን20 ሃገራት ስብሰባ በማስተጋባት የአፍሪካ ቃል አቀባይ (Spokesman of Africa) የሚል ስያሜ ያገኙ ድንቅ የአፍሪካ ልጅም ነበሩ።
21. እአአ በ1995 ዓ.ም ከዩናይትድ ኪንግደም ኦፕን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣በ2004 ዓ.ም ደግሞ ከኔዘርላንድስ ኢራስመስ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል። እአአ በ2002ዓ.ም ደግሞ ከደቡብ ኮሪያ ሃናማ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሣይንስ የክብር ዶክትሬት ተቀብለዋል።
22. ለኢትዮጵያ ልማት፣ለዓለም ሰላም፣ለምሥራቅ አፍሪካ መረጋጋት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከ10 ያላነሱ የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ከተለያዩ ተቋማት ተቀብለዋል።
Attachments
meles_zenawi.jpeg


Post Reply