የጠነባች ኢትዮጵያ

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 397
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

የጠነባች ኢትዮጵያ

Post by africangear »

ኢትዮጵያ በእምየ ሚኒሊክ ''ተከብራ'' ሳለች -ኤርትራንና ጁቡቲን ለጣልያንና ፈረንሳይ ፈርማ ትሰጣለች። ልክ እንደአሁኑ ያኔም ሙሉ ወታደር አዝምታ ትግራይን ታራቁታለች (የድንጋይ ካብ ሳይቀር አፍርሶ በመፈተሽ የትግራይ ሃብት ተዘርፏል)።

ኢትዮጵያ ''ዓለም ያስደነቀ'' ንጉስ ሲኖራት- ንጉስዋ ለባዕዳውያን ጥሏት ወደ እንግሊዝ ይሸሻል፣ ሲመለስ ደግሞ ለራስ ገዝ ኣስተዳደር (ቀዳማይ ወያነ) የሚታገለውን የትግራይ ህዝብ በእንግሊዝ የጦር ጀቶች ታግዞ ይጨፈጭፋል።

ኢትዮጵያ ለማንም ''ሳትንበረከክ'' ህዝቦችዋም ''ስለምትወድ'' --በኤርትራ እና ሶማሊያ ድጋፍ የትግራይ ክልል ህዝብን ትጨፈጭፋለች፣ ሃብት ትዘርፋለች፣ ሴቶች ትደፍራለች፣ የቀረውን ታቃጥላለች። በግብዣ የትግራይን መሬት በባዕድ እንዲገዛ ትሰጣለች። ይህም ሆኖ መሪዎችዋ ባንዳዎች ኣይደሉም። የተቀደሱ፣ ሀገር ወዳድ ናቸው።

ኢትዮጵያ ''ለምለም'' ሆና ''ጠግባ'' እያደረች--ግን ስንዴ ትለምናለች፣ ኩራት በኩራት ናት። በእርግጥ በርሃብ ሆዷ እያከከች፣ ባዶ እግሯ እየሄደች፣ በድንቁርና ብዛት ዝጋ፣ የገዛ ወገኖችዋን ''ረሃብተኞች'' ብላ ትሳደባለች።

ኢትዮጵያ ''የደጋጎች'' ሀገር ሆና እያለች ----ትግራይን ስታጥላላ እና ስትገድል ትውላለች።

17 ጊዜ ከጣልያን፣ ደርቡሽ፣ ቱርክ፣ ግብፅ ተዋግተው ያሸነፉ እና የኢትዮጵያን (ኣብሲኒያን) ሉኣላዊነትን ያስጠበቁ የትግራይ ህዝብ መሪዎች ---ለኢትዮጵያውያን ''ባንዳዎች'' ናቸው።

የኢትዮጵያ መሬት የሆነውን ጎንደርንና አከባቢው ለማስከበር የተሰዋን ንጉስ -እንኳን ክልትው ኣለ -የሚሉ ዜጎች ያላት ኢትዮጵያ አሁን ግማሽ ጎንደር በሱዳን ተይዞ ሉኣላዊ ሃገር መሆንዋን ታውጃለች፣ ጉዴ እንዳይሰማ ኣታውሩት ትላለች።

ወደ ቀድሞ ገናናነታችን እንመለሳለን ይሉና -ቀደሞ የኢትዮጵያ ገናናነት መገለጫ የሆነችውን ትግራይንና ቅርሶችዋ ያቃጥላሉ፣ ህዝቦችዋ ይጨፈጭፋሉ፣ ሴቶችዋ ይደፍራል፣ ንብረትዋ ይዘርፋሉ።

የራሷ ፊደል፣ ካላንደር፣ ያሬዳዊ ዜማ፣ ምግብ፣ ልብስ፣ ጸጉር ኣሰራር፣ ምንትሴ ያላት ሃገር ብለው ይለፈልፉ እና ---የነዚህ ሁሉ ጥንስስ የሆነች ትግራይን ማግለል ይፈልጋሉ። አግልሎ (ገድሎ) ለመጠቅለል።

በውሸት፣ ዘረኝነት፣ ዘረፋ፣ መድሎ፣ ቅናት እና ስንፍና የጠነባች ኢትዮጵያ --የትግራይን ሰዎች በነዚህ ቃላት ለመክሰስ ሞራል ኣላት። ጉድ ነው!!

ኢትዮጵያ ሀገር ስታፈር ትውልና፣ ሀገር የሚቀኑትን ወገኖችዋ ገንጣይ አስገንጣይ፣ ከፋፋዮች እያለች ትደክማለች። ጨርሳ ስትፈርስ ምን እንደምትል ደግሞ እድሜ ይስጠንና እንሰማለን!!
የተቃርኖ ሀገር!!

ትግራይ ከሀገርነት በታች አይገባትም፣ ምን ጎድሏት!!

Source: https://www.facebook.com/WoldeHagereseb ... 8333840146


Post Reply