ጀግናው ታጋይ አሞራ/ወልደገሪማ

Post Reply
africangear
Posts: 396
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

ጀግናው ታጋይ አሞራ/ወልደገሪማ

Post by africangear »

Amora-TPLF-fighter
Amora-TPLF-fighter
ጀግናው ታጋይ አሞራ/ወልደገሪማ

ጋዜጠኛ: ስምህ?
አሞራ/ወልደገሪማ
ጋዜጠኛ: እድሜ?
አሞራ: 31
ጋዜጠኛ: ተምረሃል?
አሞራ: አልተማርኩም
ጋዜጠኛ: ምን ትሰራ ነበር?
አሞራ: እረኛ
ጋዜጠኛ: እንዴት ወደ ትግል ገባህ ?
አሞራ:
1.የደርግ ወታደሮች እርጉዝ ሴትን በሳንጃ ሆዷን ዘርግፈው ህፃን ልጅ ከሆድዋ ሲወጣ አየሁ።
2. አጎቶቼ በጥይት ደብድበው ገደሉ ፤ብዙ ሰዎች በቀይ ሽብር ሲረሸኑና ሬሳቸው ተዘርግፎ አየሁ በዚህ ነው ግፍና ጭቆና ለመታገል የወጣሁ።
ጋዜጠኛ: ስንት ጊዜ ጦርነት ውስጥ ተሳትፋሃል?
አሞራ: የማስታውሰው 30 እስከ 33 ነው !በሑመራ ባዕከር 82 የደርግ መኪኖች ሲማረኩ ነበርኩኝ፡ 604 ኮር ሲደመሰስ ነበርኩኝ፡ በቆቦ በሶስት ዙር ፈንጅ የታጠረ ምሽግ ሲሰበር ነበርኩኝ፡ በድንጋይ ክምር ነበርኩኝ...
ጋዜጠኛ: ይህንን ጦርነት መቆም አለበት ብለህ ታስባለህ?
አሞራ: ይቆማል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ምክያቱም የተቆጣ ህዝብ አለ፡፡ በቀይ ሽብርና በሌሎች ምክንያቶች በጠራራ ፀሐይ እየተገደለ ያለ ህዝብ መሞት አይቀር እየተዋጋ መሞትን የሚመርጥ ህዝብ ነው ያለው፡፡
ጋዜጠኛ: እንዴት ተማረክ?
አሞራ: ለመማረክ አስቤም አላቅም ነበር፡፡ በደርግ መማረክ ለኔ ትልቅ ውርደት ነበር፡፡ ከምማረክ ይልቅ ራሴን ባጠፋ ነው ምመርጠው፡፡ ነገር ግን እጄን ተመትቼ ስለነበር ከሀይለኛ ብርድ ተዳምሮ ምንም ሳላደርግ ጓደኞቼ ሽጉጡን ቀሙኝ፡፡
ጋዜጠኛ: የምትለው ነገር አለ?
አሞራ: ለሀገር የሚበጅ ነገር ስሩ፡፡

ክብርን ሞገስን ንጀጋኑ ሰማእታትና።





Post Reply