በምዕራብ ትግራይ በ ኤርትራ ሰራዊት እና በ አማራ ክልል ታጣቂዎች በ ትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማፅዳት እና በሰብአዊነት የተፈፀመ ወንጀል

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 396
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

በምዕራብ ትግራይ በ ኤርትራ ሰራዊት እና በ አማራ ክልል ታጣቂዎች በ ትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማፅዳት እና በሰብአዊነት የተፈፀመ ወንጀል

Post by africangear »

Eritrean Troops and Amhara Special Forces killing Tigrayans in Western Tigray
Eritrean Troops and Amhara Special Forces killing Tigrayans in Western Tigray


የዘር ማፅዳት እና በሰብአዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል በምዕራብ ትግራይ (Crimes Against Humanity and Ethnic Cleansing in Ethiopia’s Western Tigray Zone)

"ከዚህ መሬት እናጠፋችዋለን(እናፀዳችዋለን)" በሚል አርእስት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሁይማን ራይትስ ዎች በጋራ በምዕራብ ትግራይ በትግራይ ህዝብ ላይ በአማራ ክልል ታጣቂዎች ማለትም "በፋኖ እና በአማራ ልዩ ሀይል" እንዲሁም በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስለተፈፀመው አረሜንያዊ የዘር ማፅዳት ዘመቻ በማስመልከት ከ240 ገፅ በላይ አዲስ ሪፓርት አውጥተዋል።
ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል በቀጥታ የመሩ እንዲሁም አምነስቲ እና ሁዩማን ራይትስ ዎች ለአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍ/ቤት ተጠያቂ እንዲሆኑ የጠቀሳቸው 3 ወንጀለኞች ደግሞ:-

1. ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ
2. ሻለቃ ደጀኔ ማሩ
3. በላይ አያሌው ናቸው።

በጥር 09/2013 ዓ.ም የተፈፀመውን "የተከዘ ወንዝ የጅምላ ጭፍጨፋ" በሪፓርቱ ላይ ከቀረቡት አንዱ ሲሆን በተከዘ ወንዝ በ60 የዓዲጎሹ ነዋሪ የትግራይ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋም አካቷል። በጊዜያዊ አስተዳዳሪዎች ማለትም እነ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የሚመሩት የጅምላ አፈሳ፣ የትግራይ ተወላጆች የሚሰቃዩበት እና የተገደሉባቸውን ሁኔታዎች በተመለከተ ከ400 በላይ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ዝርዝር ጉዳዮችን አቅርበዋል።

የኤርትራ ሰራዊት በሑመራ፣ አደባይ እና ራውያን ከተሞች ከአማራ ክልል ታጣቂዎች ጋር በመሆን የዚህ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ መሆኑንም ሪፓርቱ ያትታል። በአጠቃላይ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ህዝብ ላይ የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ የተፍፀሙ ወንጀሎችን በመስራት፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደግሞ ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ከዓለም ማ/ሰብ እንዲደበቅ በማድረግ፣ ገለልተኛ ምርመራ እንዳይኖር በመገደብ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ 15 ወራት የፈጀው ምርመራ ይገልፃል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በምዕራብ ትግራይ ህዝብ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ፆታዊ ጥቃት፣ አስገድዶ በማፈናቀል እና ሰብአዊ ድጋፍ (እርዳታ) እንዳይገባ በመከልከል በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተጋሩ ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ ማድረጉም ተነግሯል።

የአማራ ክልል አስተዳደር ይህንን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሪፓርት ተልኮለት መልስ በመጋቢት 17/2014 ዓ.ም የሰጠ ሲሆን በጎንደር ዩኒቨርስቲ አማካኝነት ህወሓት የፈፀመው የጅምላ መቃብር የሚለውን ተረት ተረት ይህንን የ240 ገፅ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሪፓርት ካዩ በኃላ እንደፈፀሙት አሁን ግልፅ ነው።

ሊንኮች:-

:arrow: አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፓርት ሊንክ: https://www.amnesty.org/en/latest/news/ ... Q4z5Cbm3fw

:arrow: ሁዩማን ራይትስ ዎች ሪፓርት ሊንክ: https://www.hrw.org/report/2022/04/06/w ... 5EV6eZlbm8

:arrow: 240 ገፅ የምርመራ ሪፓርት (PDF): Amhara to Tigray: "WE WILL ERASE YOU FROM THIS LAND"
WE WILL ERASE YOU FROM THIS LAND.pdf
(22.5 MiB) Downloaded 305 times


Post Reply