አባይ ፀሃየ ለአንድ ግለሰብ ያሰማው ታሪካዊ ንግግር

Post Reply
africangear
Posts: 396
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

አባይ ፀሃየ ለአንድ ግለሰብ ያሰማው ታሪካዊ ንግግር

Post by africangear »

ኣባይ ፀሃየ የኣክሱም ሰው ነው። እና ጦርነቱ ባይመጣና ህይወቱ በዚህ መልክ ባይቋጭ ቀሪው እድሜው ኣክሱም ሄዶ ለመኖር እያሰበ ነበር። ባለፈው የካቲት ሰሙን ለኣንዲት የቅርብ ዘመዱ ይህንን ሃሳቡን ኣጋርተዋታል። እሷም “መቐለ ኣልተስማማህም እንዴ?” ብላ ጠይቋዋለች። የሰጣት መልስ “ኣሁን ያለሁበት ቤት ተወዶብኛል። መንግስት የሚሰጠኝ ጥሮታ ሊበቃኝ ኣይችልም። ኣክሱም ብሄድ ግን የወላጆቼ ቤት ኣለ፣” የሚል ነበር። ይህ ሰው፣ በኣንድ ወቅት ኣንድያ ልጁ የልብ በሽታ ታሞበት ውጭ ልኮ ማሳከም ያልቻለ ነው። ሞንጀሪኖና እሱ፣ ለሁለት ሳይችሉ ቀርተው፣ ያሳከመላቸው፣ ባለሃብቱ የሞንጆሪኖ ወንድም ነው። በጣም ከሚያናድደኝ ነገር፣ የውሸት ክምሮች ተከምረው ተከምረው፣ የመልካም ሰው ስም ለመታደግ በጣም ኣድካሚ የሆነበት ጊዜ ነው። ኣሁን ኣባይ፣ ስኳር ምናምን እያሉ ስሙን ጭቃ ለጭቃ የሚጎትቱ ሰዎች በዝተዋል። እውነቱን የሚመረምር የለ፣ ማስረጃ ብሎ የሚጠይቅ የለ! እንደው አንድ ክፉ ሃሜተኛ ባለው ጭልጥ ብሎ መንጎድ!

አንድ አባይን በቅርብ የሚያውቅ ሰው ሰሙኑን የነገረኝ ታሪክ ነው። ፒያሳ አካባቢ አባይን “ቢልዮኖች ወስዶ ውጭ አገር አስቀምጧል” እያሉ ያማሉ። ከሚያሙት ሰዎች አንዱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ነው። መምህሩ፣ ማስረጃቹህ ምንድነው እንደማለት፣ ጭራሽ ዋናው የወሬው አጋጋይ ራሱ ሆኖ አረፈው። ሲል ሲል ይኽ ሃሜት አባይን በቅርበት ከሚያውቀው የህሜተኞቹ ጎረቤት ከሆነው ሰው ጀሮ ይደርሳል። ይኽ ሰው አባይን እንደማያውቀው ሆኖ ያዳምጣል። ወሬው አዳዲስ ግብአት እያገኘና ድራማቲክ እየሆነ ሄደ። “አባይ በ5 ወንድ ልጆቹና በ2 ሴት ልጆቹ ስም ብዙ ቢልዮኖች ዶላሮች ውጭ አስቀምጧል… ወዘተ” እያሉ ይበጠረቃሉ።ከቀናት በኋላ ይኽ ሰው አስተማሪውን ሊጋብዘው ሂልተን ይቀጥረዋል። ከጥቂት ደቂቃ በኋላም አባይ ጸሃየ ይመጣና ይቀላቀላቸዋል። አባይ አስተማሪውን አያውቀውም። አስተማሪውም በሚድያ አደባባይ ካልሆነ አባይን በንደዚህ ቅርበት አያውቀውም። እዚያው ነው ያስተዋወቃቸው። ያ አስተማሪ ከአባይ እንደሚገናኝ ባያውቅም አባይ ግን ጊዜ የመደበለት ቀጠሮ ነው። ስለዚህም “ተዋወቁ” ሲባል “አይ እኔ አስመላሽ እባላለሁ (ስም ተቀይሯል)፤ አስተማሪ ነኝ። ክቡር አቶ አባይን እንኳን አለማወቅ አይቻልም። ከአቶ መ*** በቅርብ ነው የተዋወቅነውም የተቀራረብነውም። ከርስዎ ጋር እንደሚተዋወቅ ግን አልነገረኝም። የርስዎን ስም እያነሳን ስናወራ ሁሉ ከርስዎ ጋር እንደሚተዋወቅ አልነገረንም። እዚህም ልግብዝህ ብሎ ቀጠረኝ እንጂ እርስዎ ጋር እንደምንገናኝ አልነገረኝም። ትንሽ ግራ ገብቶኛል፤ ይቅርታ ያድርጉልኝ…” አለ አስተማሪው። መጠነኛ ፍርሃትና ግራ መጋባቱ እንዳያስታውቅበት ራሱን እየተቆጣጠረ። ከዛ በኋላ የተናገረው አባይ ነበር…

“ጥሩ ነው። በበኩሌ ስለተገናኘን ደስ ብሎኛል። ሃሳቡ የመጣው ከመ*** ነው። እኔም ተስማማሁ። የተስማማሁት ለኔ ለግሌ ጥቅም አለው ከሚል ነው። ብዙ አትጨናነቅ፣ ከሆነልን ጉደኞች እንሆናለን። ካልሆነም በመገናኘታችን የምናጣው ነገር የለም። የኔና ያንተ እድሜ የሚቀራረብ ይመስለኛል። ምናልባት በጥቂት እበልጥህ ይሆናል። በዛ ላይ ራሴን እንደ እድሜ ልክ ታጋይ ነው የማስበው። ለመቀራረብ እንዲረዳን አንቱታው ይቅርብን። ካንተ ጋር በደንብ መተዋወቅ ላንተ ካለው ጥቅም ለኔ ያለው ይበልጣል። ምክንያቱም እኔ ስላንተ ምንም የማውቀው ነገር የለም። አንተ ግን ስለኔ ጥቂት ነገሮች ታውቃለህ። ብዙዎቹ በቅብብሎሽ የተገኙ የተሳሳቱ ናቸው። ለምሳሌ እኔ ሰባት ልጆች የሉኝም። ያለኝ በትግል ጊዜ ሜዳ ላይ የተወለደ አንድ ልጅ ብቻ ነው። የልብ ህመም ገጥሞት ጦር ኃይሎች ተኝቶ ነበር። በመንግስት ባለስልጣንነቴ ያገኘኋት ጥቅም ይች ናት። ልጄን ጦር ኃይሎች ማሳከም መቻሌ። ከዛ ግን ውጭ ካልሆነ ተባለ። እንደሚወራው አይደለም። በልጄ ወይም በራሴ ስም የተከፈተ አካውንት ወይም የተቀመጠ ገንዘብ የለንም። በእናቱም በኩል እንዲሁ። ሙዳዬ ምጽዋት ይዙር ምናምን ሲባል፣ የእናቱ ወንድም፣ አጎቱ ደረሰልን። በዚህ መልክ ነው የታከመው። እኔ አሁን ነገ መንግስት ከስራ ያለ ጡረታ ቢያባርረኝ፣ እኔ ከኪራይ ቤት ልቀቅ ብባል፣ አንድ ወር እንኳን መዝለቅ ሊከብደኝ ይችላል። እኛ አየህ.. ራሳችንን እንደ አብዮታውያንና ህዝባውያን ታጋዮች ነው የምናየው። ሁሌም በኛ የእለት እለት ህይወት ቅድሚያ የሚይዘው ዓላማውና የሰማእታት አደራ ነው። በስርአታችን ያለው ሙስና እኛን ተጠግተው በሚበለጽጉ ሰዎች የሚከናወን ስለሆነ በፍጥነት ማስወገድ አልቻልንም። ሙስናና ሌብነት ብዙ መገለጫ ያለው የከተማ ሰው ባህርይ ነው። ከጫካ ብንመጣም አደገኛ ጫካ የሆነብን ከተማው ነው። አሁን አንተ የሰማሃቸው ወሬዎች የሚያሰወሩት ስርዓታችን ውስጥ እየሞሰኑና በሙስና እየበለጸጉ ያሉት ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ነገር ህግና መልክ እንዳይይዝ ችግር የሚፈጥሩ እነሰው ናቸው። አንዱ ዘዴያቸው እነዚህ የስም ማጥፋት ወሬዎች ናቸው። ህዝባችንም ተመቸላቸው፤ ለወሬው እንጂ ለማስረጃ ግድ የለውም። …”

አባይ፣ ለአንድ አስተማሪ እውነቱን ለማስጨበጥ በግል ያደረገው ጥረት እናያለን፣ እናደንቃለን። ከዚያ በኋላ የሁለቱ ጓደኝነት እንደቀጠለ ይገመታል። አስመላሽ፣ ከነዛ ሃሜተኛ ጓደኞቹ ሲቀላቀል “አባይ እናንተ እንደምታስቡት አይነት ሰው አይደለም፤ ፍጹም ልዩና ትሁት ነው። ስሙ በተለያየ መንገድ በመጥፎ የሚነሳውም በስህተት ነው” ማለት እንደጀመረ ተሰምቷል። ጎሽ! አባይ ጓደኛየ ነው እያለ የጋባዦች ቀልብ መሳብ ጀምሮ እንደነበረም ወፍ ነገረችን። ምን ተሻለ? አሁን አባይ በዚህ መልክ በግፍ በጨካኞች እጅ ሲገደል ግን አስመላሽ ምን ይል ይሆን የሚለው መላምት ያጓጓል። ይህኔ እንደገና ተከርብቶ “ሂልተን ጠርቶ ሊያስፈራራኝ ሞከረ፣ ተላላኪ ሊያደርገኝ፣ ሊመለምለኝ ሞክሮ አልተሳካለትም… ምናምን” ይልልኝ ይሆናል። ይኽ የማህበረሰብ እሴት መላሸቅ ዋና ማሳያ ሆኖ የወጣ ይመስለኛል።

ኣባይን ኢቲቪ በነበርኩበት ጊዜ ኣንዴ ለግንቦት 20 በኣል ልዩ ዝግጅት ኢንተርቪው ኣድርጌው ኣውቃለሁ። ያኔ ውስጤ የቀረች ትዝታ ትህትናው ናት። ሲበዛ ትሁት ነው። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ደግሞ የኣሰር መጽሄት ዋና ኣዘጋጅ ሆኜ ነበር፣ ለኣጭር ጊዜ። ለመጽሄቱ ልዩ እትም፣ እኔና ኣታኽልቲ እምባየ፣ ስዩም መስፍንንም፣ ኣባይ ጸሃየንንም ኣነጋገርን። ስለጦርነቱ ነበር። የሁለቱ ስእል ሽፍኑ ላይ እንዲወጣ ተስማማን። ኣቀማመጡ ላይ “የማናቸው ከላይ ይሁን” በሚለው ግን ከኣታክልቲ ጋር በትንሹ ተጨቃጭቀን ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጎላ ያለ ባለስልጣን ነው። ኣባይ ያኔ በመንግስት ደረጃ የሚታወቅ ፖርቶፎልዮ ኣልነበረውም። የኣታኽልቲ ክርክር፣ ፓርቲው ላይ ባለው መዋቅር “ኣባይ ይበልጣል” በሚል ነው። መጽሄቱ የፓርቲው ስለሆነ ይሆናል እንደዛ ያሰበው። በመሃል እንደመሳቅ ብየ “ይሁን” ስለው፣ “ምንድነው ያስፈገገህ?” ኣለኝ። ካልነገርኩት የማይለቀኝ ወይም ቅር የሚለው መሰለኝ።

“ኣይ፣ እነሱ ታጋዮች ናቸው፣ ፕሮተኮል ጉዳያቸው አይደለም። ይህን ጭቅጭቃችን ቢሰሙት ምን ይሉ ነበር፣ ብየ ነው።”
“እኛ ለነሱ ስሜት ብለን ኣይደለም፣ ኣሰራሩ ነው፤” ኣለኝ ቆፍጠን ብሎ።
ከዚያ በኋላ ኣባይን ያገኘሁት በ1998 ዋሽንግተን ዲሲ ነው፣ ኢምባሲው ዉስጥ ኢትዮጵያውያንን ሰብስቦ ሲያናግር። ከቀረቡለት ጥያቄዎቹ ኣንዱ “ቅንጅቶች ኣንረከብም እሳካሉ ድረስ፣ ኣዲስ ኣበባን ለባለ ኣደራ መንግስት የሰጣቹሁት ለምንድነው?” የሚል ነበር። ኣባይ የሰጠው ምላሽ፣ የፓርቲውን ህዝባዊነት የሚያሳይ ነበር። “እኛ ከኣዲስ ኣበባ ህዝብ ጋር ተቆራርጠን መቅረት ኣንፈልግም። በሚቀጥለው ኣሻሽለን፣ እንደገና ተወዳድረን የኣዲስ ኣበባ ህዝብ እንዲመርጠን እንፈልጋለን፣” ሲል ተናገረ። አሁን እንዲህ አይነት ንግግሮች ከመሪዎች መጠበቅ ቅብጠት ነው። “ድምጽህ ከነፈግከኝ፣ እና ድምጽህ የሰጠኸው ፓርቲ አልረክብም ቢልም ባልመረጥከው ሰው አትተዳደርም፣ ለአጭር ጊዜ በባለአደራ ቆይተህ የራስህ አስተዳዳሪዎች ትመርጣለህ” ነበር ሃሳቡ። አሁንስ? ለመረጥከው መንግስት እውቅና መከልከል አይደለም፤ የተመረጠውን መንግስት በጦርነት አስወግዶ የራስ ተላላኪ ሹመኛ ማስቀመጥ አይደለም፤ ጭራሽ አረመኔ የለየለት የጠላት መንግስት ጋብዞ “እንዳሻህ ግደላቸው፣ ዝረፋቸው፣ አውድማቸው… “ ብሎ አሳልፎ መስጠት፣ ይህ በታሪክ ተፈጽሞ የማናውቀው ወንጀልና ክህደት ነው። ይኸም አልበቃም፤ ሁሉም ነገር ተዘግቶበት በረሃብና በበሽታ እንዲያልቅ በትጋት እየተሰራበት ያለ ህዝብ ነው። የትግራይን ህዝብ በመግደል ለመገላገል ያለው ጥድፊያ ልዩ ነው። የነ አባይ ጸሃየ ርሸናም የዚያ አካል ነበር።

በዩኒቨርሲቲው ጊዜ አባይ ጸሃየ (ያኔ፣ አመሃ)፣ እጅግ ትንታግ ከሚባሉት ልበ-ብሩህ ተማሪዎች አንዱ ነበር። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚያዘጋጀው Struggle የተሰኘ የታወቀ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበር። ለትግል ቀድመው ሜዳ ከወጡት ተማሪዎች አንዱ ነው። በሰላሙ ጊዜም፣ የህወሓት ትግል የላይኛው አመራር ሰው ሆኖ ዘልቋል። ከህወሓት በክብር ከተሰናበተ ጥቂት አመታት ሆኖታል። ከመንግስት ኃላፊነትም ጥሮታ ከወጣ ወደ 3 ዓመት እየተጠጋ ነበር።

መጽናናት፣ ለትግራይ ህዝብና ለወዳጆቹ!
ትግራይ በመስዋእትኹም ትነብር፣ ትግብል!


Post Reply