ጩኸት የሚቀሙ የሞት ነጋዴዎች
Posted: Fri Jan 22, 2021 8:13 am
'እናውቃለን እንደሚባለው 4.3 ሚሊዮን ባይሆንም 2.5 ሚሊዮን ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ አሉ'፣ 'እከሌና እከሌ - - - ድጋፍ ሰጡ' እያሉ ማላገጥ ጀምረዋል::
እንደው ፈጣሪ ያሳያችሁ በሚሊዮን ያፈናቀሉን እነሱ፣ በሺዎች እንድንሰደድ ያደረጉን እነሱ፣ በሺዎች እንድንታረድ ያደረጉን እነሱ፣ የወረሩና ያስወረሩን እነሱ፣ በሺህዎች የደፈሩና ያስደፈሩ እነሱ፣ የሚገሉንና የሚያስገድሉን እነሱ፣ የሰረቁና የሚያሰርቁን እነሱ፣ አለምአቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች እንዳይገቡ የከለከሉ እነሱ፣ አለምአቀፍ ጋዜጠኛ እንዳይገባ የከለከሉ እነሱ፣ ነጻ እርምጃ (ርሸና) የሚወስዱና መውሰዳቸውን እንደጀብዱ የሚደሰኩሩ እነሱ፣ መሠረተ ልማቶቻችንን ያወደሙ እነሱ፣ ቅርሶቻችንን የሚዘርፋና የሚያወድሙ እነሱ፣ ምስለኔ ባንዳዎችን ገዥ አድርገው የሚሾሙ እነሱ፣ የትግራይን መሬቶች ለሻዕቢያና ለትምክህተኞች አስረክበው ህዝቡን የሚያሰቃዩ እነሱ - - -የትግራይ ሴቶች ደፍረው የሚጎረሩ እነሱ፣ . . . እነሱ ያላደረጉት ምን አለ?
ገዳይ እንደምን አዳኝ፣ የችግር ምንጭ እንደምን የመፍትሔ አካል ሊሆን ይችላል? የትግራይን 4.5 ሚሊዮን ህዝብ ለረሃብ ያጋለጠ - ጠቅላላ 12 ሚሊዮን የትግራይን ህዝብ የሃዘን ማቅ ያለበሰ የአራዊቶች ስብስብ እንደምን የሰብዓዊነት ስራ ሊሰራ ይችላል?
ከሰራቂው ጋር ሆኖ ንብረቱን የሚፈልግ ባለንብረት እንደምን ንብረቱን ሊያገኝ ይችላል?
የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት፣ ለማደህየትና ለማንበርከክ የተጀመረውን ወረራ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የደገፋችሁ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ተቋማቶች፣ ድርጅቶችና ስብስቦች ሁሉ የአዞ እንባና ጩኸታችሁን አንሻም! የኛ ፍላጎት አንድና አንድ ነው! ውጡልን! ውጡልን! ውጡልን! ተውን - ተውን + ተውን!
የትግራይን ህዝብ ለመርዳት የሚፈልጉ:-
1ኛ. ሚሊዮኖች ተጋሩ አሉና የዘጋችሁትን መንገዶች ክፈቱ - ኔትወርኩን መልሱ - ባንኩን ክፈቱ።
2ኛ. ከ52,000 ሺ በላይ ያሰሯቻቿውን የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች፣ ታጋዮች፣ የደህንነት ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች፣ ጋዜጠኖች፣ ተራ ነዋሪዎች፣ - - - ፍቷቸው
3ኛ. በየትኛውም የተቀረው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የትግራይ ተወላጆችን ንብረት ያገዳችሁትን አንሱ!
4ኛ. ቀን ከለሊት ስለትግራይ የሚጨነቁ የሰብዓዊ እርዳታ ለመስጠት በተደጋጋሚ ጠይቀው የተከለከሉ ድርጅቶች እንዲገቡ ይደረግ::
5ኛ. የተወረሱ የትግራይ ህዝብ ንብረቶች ይመለሱ - በተለይ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶቻችን ለአለም አቀፍ ድርጅቶች በነጻም ቢሆን አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረግ::
ከዚህ ውጪ የቁራ ጩኸት አያሻንም! ማንም የትግራይ ህዝብ ወዳጅ ነኝ የሚል ግለሰብ፣ ቡድንም ሆነ ተቋም ከነዚህ ነጥቦች ውጪ ቢያነሳ አስመሳይነትና ገረድነት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል:: ሌላውን ፍላጎታችን በትግላችን እናረጋግጣለን::
Ezana Oscar