Page 1 of 1

የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ - ነሓሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም

Posted: Tue Aug 17, 2021 8:49 am
by africangear
mengistu-hailemariam.jpg
የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ
ነሓሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም

የዛሬ ውሎዬን ምኑን ዋልኩት! ጥላየ እንኳን ሳይቀር ቀን እየጠበቀ ላብ እስኪያጠምቀኝ ያስፈራራኛል፡፡ ዕድሌ ነው! ሌላው የታደለው ዱቄትማ፤ ክላሽን ይዞ፤ ከታንክና መድፍ ጋር ሳይቀር ተናንቆ ይማርካል፡፡ ይኸው ዛሬ እንኳን 11 ታንክ 11 መድፍ ማረኩ አይደል! እነሱ ደግሞ ይህ 11 ይሆናቸዋል፡፡

“ዕድሜያችሁና ዓቅማችሁ የሚፈቅድላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዝመቱ” ነው ያለው ልጅየው! “የመከላከያ ሠራዊቱን፣ ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻውን እንድንቀላቀል!” ከዚያ ጦር ሜዳ ሊኬድ! አላደርገውም! እግሬን አላነሳም! ብቻየን ስብሰለሰል ነው የዋልኩት፡፡ ዕድሜ ወደፊት ወይ ወደኋላ የሚገፋ ቢሆን ኖሮ፤ ምንኛ ደግ ነበር፡፡

የጁንታው ሰራዊት ውጫሌ፣ ሃይቅ፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ታየ ደረሰ መባሉ ሳያንስ፤ ኦነግ ሸኔ አዲስ አበባን ዙሪያዋን አንቆ ሲጥ ሊያደርገን፤ የሁለት ሳምንት ጊዜ ስጡኝ በሚልበትና፤ ከወዲሁ የጎጃም-ቡሬ-ነቀምትን መስመር ሆሮጉድሩ ላይ በዘጋበት በዚህ ወቅት፤ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ዘመቻ!

ደግሞ እኮ ከጁንታውና ከኦነግ ሸኔ ጋር ብቻም እኮ አይደለም፤ “ትግላችን ከአሸባሪው ጁንታ ጀርባ ላይ ተፈናጥጠው፤ ሀገራችንን ለማፈራረስና የኢትዮጵያን ህልውና ለማጨለም፤ ከተነሡ የቅርብና የሩቅ ኃይላትና አገራት ጋር ጭምር ነው!” ይላል መግለጫው፡፡ “የሩቅ ኃይላትና አገራት!” ጉድ በል ጎንደሬ! የቅርቧ ሱዳን ብቻ መስሎኝ ነበር፤ ለካስ የሩቋ አሜሪካም አለችበት! ያልማል ይቃዣል ወይም ሕዝቡን ያሞኛል!

አዲስ አበቤዎችማ፤ እንደዚያ የቀን ጅብ ብለው እንዳልተሳለቁበትና፤ ደረታቸውን እየደቁ መከላከያውን አሰንቀው አስታጥቀው መርቀው፤ እንደላዘመቱበትና እንዳለስጨፈጨፉት፤ “አረ እነዚህ ሰዎች ቶሎ መጥተው በገላገሉን” ማለትም ጀምረዋል፡፡

የጨቅላው መግለጫ የመጨረሻዋ ዓረፍተ ነገር ሳልወድ በግድ በፍርሃቴ ውስጥ ፈገግ እንድልና ስለልጁ እንዳፍርለት አስገደደችኝ፡፡ “የእኛም ስም በታሪክ መዝገብ በጀግንነት ተመዝግቦ ይኖራል” የሚለውን ደጋግሜ አነበብኩት፤ “በጀግንነት” የሚለውን ቃል አሳስቼ አንብቤው እንዳይሆን ብየ፡፡

“የሃይማኖት አባቶች በጸሎት፣ የአገር ሽማግሌዎች በምክር፣ ሁሉም ዜጋ በችሎታው ኢትዮጵያን ብሎ ይቁም!” የምትለዋ ተመችታኛለች፡፡ አሁን ነው የቤተክርስትያን ሰባኪ አገልጋይ መሆን! ነገ እንዲያውም ኣቦየ ናቸው!
አዲስ አበቤው ነኝ፤ ለማንኛውም የነገ ሰው ይበለን!