የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ - ነሓሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም
Posted: Tue Aug 17, 2021 8:56 am
የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ
ነሓሴ 6 ቀን 2013 ዓ.ም
ትናንት ማታ በከተማይቷ የተረጨው ሳኒታይዘር፤ ከአናት የሰፈሩባትንና ከጀርባዋ ተጣብቀው የሚመጠምጧትን፤ ተውሳከ ብልፁጋን ህዋሳቶችን ያስደነገጠና ኩምሽሽ ያደረገ ነበር። ከርጭቱ ብዛት የተነሳ በአንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የጤና መታወክ አስክትሏልም የሚሉ አሉ፡፡ የእኔ ቢጤ አኗኗሪው ብዙሓን ማሕበረሰብ ውስጥ ግን ጤናንና አግራሞትን ጭሯል፡፡
“ሳኒታይዘር ቢሉኝ፣ የኮቪድ ነው ብዬ፤
ሳኒታይዘር ቢሉኝ፣ አልኮሉ ነው ብዬ፤
ለካስ ያበሎም ነው፣ አረ እናንተ ሆዬ!”
እንዳለው ባለማሲንቆ፤ እኔም ሳኒታይዘሬን ተቀብቼ፤ ጃንጥላዬን እንደዘረጋሁ ወደ አውቶቡስ ማቆሚያው በዝግታ ሳዘግም፤ ዛሬም ያ ኮልኮሌ የሰፈራችን ፖለቲከኛ ከፊት ለፊቴ ግትር አለ፡፡ ሊያረዳኝ! “ሰምተሃል?” አለኝ፡፡
“ምኑን?” ብለው፤ “ለአገሪቱ ብልፅግና ጠንቅ የሆኑ ሁሉ፤ ዕጣ ፈንታቸው ይኸው ነው!” አለኝ፤ ስለምን እንደሚዘባርቅ አልገባኝም፡፡ “ስለምን እያወራህ ነው? እባክህ ዞር በልልኝ፤ ስራ ረፍዶብኛል” አልኩት በምን ዓቅሜ ልገፋው፤ ግን ማለፊያ ካገኘሁ ብዬ ግራ ቀኙን አማተርኩ፡፡
“ጉድሽን አልሰማሽማ፤ ወዳጅሽ አብዱልጀባር፤ ማን እንደሸኘው ሳይሰናበትሽ ሄደ” አለኝ፤ አፉን ሞልቶ፡፡
“አብዱልጀባር ማን? አብዱልጀባር ሁሴንን ነው? ወዴት ነው የሚሄደው?” ስለው፤ ወደ ሰማይ ቤት አመላክቶኝ ጥሎኝ ሄደ፤ ደስ ብሎታል፤ ገፅታው በፈገግታ ተሞልቷል፡፡
በብዙ አጋጣሚ ስለማውቀው ሐዘኔ በረታ! አብዱልባጅር ድሃ ሲበደል ፍትህ ሲጓደል መመልከት የማይሻ፤ እውነትን ይዘህለት እስከሄድክ ድረስ፤ ስለሰው ልጅ መብት እንጂ፤ ማንነት ሃብትና ፆታ ሳይለይ ጥብቅና የሚቆም፤ ቅን ሰው እንደነበር፤ እኔ ብቻ ሳልሆን፤ ብዙዎች የቆመላቸውና ተሟግቶ ነፃ ያወጣቸው ይመሰክሩለታል፡፡ በዓይነ ህሊናዬ ተጓዝኩ፤ ዓይኖቼ በእንባ ተሞሉ፤ ቀጣይ ተረኛ የዘንዶው እራትስ ማን ይሆን ብዬ ለአገሪቷም አነባሁ፡፡
አውቶቢሱ እስኪመጣ ድረስ፤ መጠበቂ መቆሚያው አጠገብ ጥግ ይዠ ስበግን ስፍተለተል፤ ስልኬ ድምፅ አሰማ:: ሩዋንዳ ካለው ጓደኛዬ የተላከ የሜሰንጀር መልዕክት ነው፡፡
"ደግሞ የእናንተ ሰውዬ እኛ አገር ምን ይሰራል" ቢለኝ፤ እባቡ መስሎኝ፤ "ግዳይ ጥሎ ወደ ውጭ መውጣት ዓመሉ ነው፡፡ ልክ ስመኘሁን እና ሌሎችን ግዳይ ጥሎ ወደ ውጭ አገር በመሸሽ አልነበርኩም እንዳለው፤ ዛሬ ደግሞ አብዱልባጅር ሁሴንን ስለጣለው ይሆናል" አልኩት፡፡ "እስከ ሃይቅ ወሎ የነበረው በሰሜን እዝ አምሳያ ያቆመው ጦሩ መደምሰሱን ሰምቶ፤ እያመለጣቸውም ይሆን?"ብለው፤
"አንተ ደግሞ የትና የት ነው የምትዘባርቀው! እኔ ያልኩት የቀድሞውን ባለ አራት ዓይን ነው፡፡ አብዱልባጅር ምን ሆነ?" አለኝ፤ አረዳሁታ፤ እኔስ መንገድ ላይ አይደል የተረዳሁት፡፡ የሁለታችንም ወዳጅ ነበር፡፡
"ኃይለማሪያምን ነው እንዴ?"
"አዎ ኪጋሊ ሩዋንዳ ላይ ከሙሉዓለም ስዩም ጋር ሲገለፍጥ አየሁት" ቢለኝ፤ የዚህ ሁሉ ዕልቂት ጥፋትና የአገር ውድመት ጠንቅ መሆኑ ታይቶኝ፤ "የዘንዶው ልዩ መልዕክተኛም አይደል! የዘር ጭፍጨፉውን ከሩዋንዳ ተሞክሮ ወስዶ ሊመለስ ይሆናላ" አልኩታ!
አውቶቢሷ ስትመጣ ጠብቄ ገባሁ፤ የሙቀት ወላፈን ከበር ይቀበልሃል፡፡ ከባሱ ውስጥ እንኳንስ መቀመጫ ልታገኝ፤ አደላድለህ የምትረግጥበት መቆሚያም የለም፡፡ እንደምንም ተደጋግፌ ተገፋፍቼ በሕብረት ጉዟችንን ቀጠልን፡፡
"አረ ታፈንን..." የሚል የአንድ እናት ድምፅ ከጫጫታው ጎልቶ ይሰማል፡፡
"አዎ ታፈንን እባካችሁ... ለንፋስ መውጫ እንኳ መስኮቱን ክፈቱት" አለች አንዷ ቅንጥስጥስ ያለች ለግላጋ ወጣት፡፡ እኔው ፊት ለፊት ብትሆንም፤ በሁለት ዓይኔ ሙሉ ሴት ልጅን ማየት ባለመቻሌም አይደል፤ ይኸው ቆሜ ከወላጆቼ ቤት የቀረሁት፡፡
በያዘችው ወረቀት ፊቷንና ምልምል አንገቷን እያራገበች፤ የሰውን ትኩረት ለመሳብ በሚመስል ከምጥን ፈገግታ ጋር ዓይኖቿ ክብልል እያሉ፤ ወደ ሁሉም አቅጣጫ ያማትራሉ፡፡
"በሷ ቤት ቅኔ መሆኑ ነው እኮ" አሉኝ፤ አንድ በዕድሜ ገፋ ያደረጉ የተደገፍኳቸው አባት፡፡
"እንዴት?" ብላቸው፤ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብለው፤ "ጀንታዎቹ ጋይንት ነፋስ መውጫ ደረሱ እየተባለ አይደል፤ እሱኑ ወሬ በነገር እየወጋች መሆኑ ነው" አሉኝ፡፡
"እነዚህ ሰዎች እኮ ጂኦግራፊ መምህራችን ሆኑ! በቀን አራት አምስት የቦታ ስም እያስጠኑን፤ አገርህን እወቅ ፕሮግራም አደረጉት እኮ! ንፋስ መውጫ ደግሞ የት ነው?" ብላቸው በገፅታቸው ክፉኛ ገሰፁኝ፡፡
"ጤና የለህም እንዴ! የፋና ወይ የዋልታ ዜና የምታወራ መሰለህ እንዴ ጮክ ብለህ የምትተረተረው!" ብለው፤ ይበልጥ ወደ ጆሮየ አስግገው፤ "ንፋስ መውጫማ በወረታ በደብረታቦር ስትሄድ ለጥቀህ የምታገኘው የጋይንት ዋና ከተማ ነው" አሉኝ፡፡
በለሆሳሳ ድምፄ፤ "ወረታ ደብረታቦርስ የት ነው?" ብላቸው፤ ብርክ እስኪይዘኝ ድረስ ቀልቤን ገፈፉት፡፡
"ወዲያልኝ! እዚያው ሂደህ ጠይቅ! ተናግሮ አናጋሪ ልክፍት! ምን ያደርቀኛል!" ሲሉኝ ጮክ በማለታቸው፤ ሌባም መስያቸው ነው መሰለኝ፤ የሰው ዓይን ሁሉ እኔው ላይ ተረባረበ፡፡ የፈረደብኝ! የሰው ዓይን እንደ ጦር ይወጋል የሚሉት ብሂል እኔ ላይ ደርሶ፤ ስራ ቦታ ከመድረሴ በፊት አቋርጨ ወረድኩ፡፡
ጥሩነቱ ስራ ከመግባቴ በፊት እግረ መንገዴን የወር ደመወዜን ለማውጣት፤ ወደ ባንክ ጎራ አልኩኝ፡፡ "ብር አልገባልህም" አለችኝ የባንክ ሰራተኛዋ፡፡ ስላልገባኝና ጆሮየንም ስለተጠራጠርኩት፤ "እባክሽን ድጋሚ እስቲ እይልኝ" አልኳት፡፡ መልሷ ያው ነው፤ "አይዞህ በአገር የመጣ ነው" በሚል አተያይ፤ "አልደረሰም" ስትለኝ ሆድ ባሰኝ፡፡
"አረ ጓዶች ይሄ ነገር ምንድነው? ወሩ ከገባ እኮ ስድስት ቀን አለፈው!" ፈርዶባት፤ እሷ ከኪሷ የምትሰጠኝ ይመስል፤ እሷ ላይ ጀግኘ፤ እኔም በዓቅሚቲ ቧረቅኩባት፡፡ ግን ምን ላድርግ፤ ጨንቆኝ ነው፡፡
አንዱ ከበስተግራየ ይንጎራደድ የነበረ የባንክ ደንበኛ ቀረብ አለኝና፤ "ይኸውልህ፤ ሕጋዊ ሰነድ ጨርሼ፤ የባንክ ብድር አልቆልኝ፤ ለመበደር ብመጣ ከለከሉኝ" አለኝ፤ የመኪናውን ቁልፍ ጣቱ ላይ እያሽከረከረ፤ ብስጭትጭት ብሏል፡፡
"እናቱ የሞተችበትም፤ እናቱ ወንዝ የወረደችበትም፤ አብረው ያለቅሳሉ አሉ! እኔ ከወር ወር የማትዘልቀውን፤ ከእጅ ወደ አፍ የሆነችውን ቅርሴን ነው ያጣሁት!" እያልኩኝ በውስጤ ሳጉረመርም፤ ለካ ድምፅም አውጥቸ ነበር፡፡ ያ ብድር አጣሁ ያለ የመኪና ቁልፍ የሚያሽከረክር መኪና የሚያህል ሰው፤
"ምን እያልክ ነው የምን የሃበሻ ምቀኝነት ነው!" ቢለኝ፤ ከአውተቡሱ የተረፈችው እራፊ ቀልቤ ተሟጠጠች፡፡ ምን እንደምመልስለትም ወይ እንደመለስኩለትም አላውቅም፤ ብቻ ውልቅ ብየ በፍጥነት ወደ ቢሮ ማምራቴን ነው የማስታውሰው፡፡ ምነው ፈጣሪ፤ ስለምንድነው ሁሌ አስፈሪ ሰዎችን ሁሉ፤ በእኔ ላይ የምታሰማራብኝ!
ከቢሮ ውስጥ ብዙ ሰዓት ብቆይም፤ የስራ ቦታችን ተቀዛቅዟል፡፡ እውነትም ሰው ብርዱን መቋቋም አቅቶታል፤ ግን የውጭው ብርድ ብቻም ሳይሆን፤ የውስጥ ብርዱም ተደማምሮ አይሎበታል፡፡ ለካስ ሁሉም በጥዋቱ ባንክ ተሳልሞ ነው የመጣው፡፡ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ሰው ፍልሰታን እያስቀደሰ ያለው ባንክን በመሳለም ሆኗል፡፡ ምሕረቱን ያውርድልን፡፡
እንዲሁ በጣምራ ብርድ ተቀፈደድን እንደተፋዘዝን፤ ድንገት ከአዳራሹ መሃል ካለው የቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያለችው፤ ካናዳዊቷ ቢለይኔ ስዩም፤ "የሕወሐትና የሸኔ ጥምረት ለፌዴራል መንግስት ምንም አላስገረመውም" የሚል መግለጫ መስጠት ጀመረች፡፡ ከአጠገቤ ያለው ባልደረባዬ ሻይዩን ፉት እያደረገ፤ "እናማ ከላስገረማችሁ፤ ስለምን መግለጫ ትሰጣላችሁ" ብሎ ፈታ ሊያደርገን ሞከረ።
የነገው ስላሶች ከሁሉም በላይ ለኢትዮጵያ ባንኮች በረከታቸውን ያውርዱልን! እባካችሁን አሜን በሉ! ካልሆነ ቅዳሜና ዕሑድን ማለፊያ መሻገሪያ የለንም፡፡ ያ የእነ በሎም ሳኒታይዘር በቀናት ውስጥ ካልሆነ በሳምንታት ብሎ ወደላይና ወደ ታች የለቀቀብን ይበቃል፡፡ የትናንትናዋ ነብይ ብርቱካንም ሆኑ፤ ዛሬ ዋናዋ መሪ ፀላይ ናቸው የተባሉት ነቢይ ቀለሟ፤ አደራ ለባንኮቻችን ይፀልዩ!
አዲስ አበቤው ነኝ፤ የነገ ሰው ይበለን!