የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ - ነሓሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም
Posted: Tue Aug 17, 2021 8:45 am
የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ
ነሓሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም
በዕለተ ሰንበት በጠዋቱ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ፤ የስራ ባልደረባዬ የአጭር የስልክ መልዕክት ድምፅ ነበር፤ "እንኳን ለ43ኛው የአብቹ የድጋፍ ሰልፍ አደረሰህ" ይላል፡፡ በጥዋቱ መስሪያ ቤት ተገኝተን፣ ስማችንን አስመዝግበን፣ የግዴታ የድጋፍ ሰልፍ እንድናደርግ ቀጭን ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ "ካለበለዚያ ዋ!" ተብለናል:: በጥሩው ዘመንማ የፍልሰታን ሰንበት ከእነአባየ ጋር አስቀድስ ነበር:: አሁን እሁንማ እኮ እንደ ሕዝብ የእራሳችን የምንለው ሰዓት እያጠረን ነው:: በታዘዝነው ቦታ ሁሉ ተገደን መገኘት አለብን::
የኢትዮጵያ ችግር በሰልፈኛና በፈረሰኛ ይፈታ ይመስል፤ ጊዜያችንን ዓቅማችንን ጨረስን፡፡ በሌሊቱ መስቀል በአደባባይ የታጎረው፤ ከተለያዬ መስሪያ ቤትና ከየቀበሌው በግዳጅ የከተተው ህዝብ፤ አብዛኛው በወሬ ተጠምዶ ይንሾካሾካል፡፡ አዘጋጆቹ ሕዝቡን በአገር ስሜት ለማስከር የጥላሁን ገሰሰን ሙዚቃ ለቀውታል፡፡
አብረን የምንጋልበው የጋራ ፈረስ በሌለበት፤ እንደምን አገርን መታደግ ይቻላል እንጂ፤ እስከ ሁለት ሺህ ብር አበል ጎርሰው የከተቱት የኦሮሚያ ፈረሰኞች፤ በግል እየጋለቡ ነው፡፡
"ሁነኛ ጋላቢ ቢያገኝ ኖሮ ፈረስ፣
መች ይጠብቅ ነበር እስኪገርፉት ድረስ" አይደል ብሂሉ!
ከጓደኛየ ጋር እየተጓተትን ባለፍን ባገደምንበት ሁሉ፤ የከተተው ሰልፈኛ ሁሉ ስለጦር ሜዳ ነው የሚተርከው፡፡ ንፋስ መውጫ፣ ደብረታቦር፣ ላሊበላ፣ ጭፍራ፣ ሚሌ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ወዘተ… የሚል ድምፅ፤ ጦርነትን ለመመከት ለመዝመት በመስቀል አደባባይ በተገኘው ሕዝብ፤ ይነሳል፣ ይስተጋባል፣ ይወቀጣል፡፡ ጁንታው የት ደረሰ ነው ነገሩ፡፡
ጓደኛየ ጋር አለቃችንን አፈላልገን ፊታችንን አስመታን፡፡ ከዚያ በኋላማ የነበረውን ዲስኩር እኔ በምን አንደበቴ ልድገመው! ግን ማን አዳምጦት! የጥላሁን ሙዚቃ ግን ጎላ ብሎ ተሰምቷል፤ "ጠላትሽ ይወድቃል ከእግርሽ" ድሮ ድሮ ይህንን ሙዚቃ ስሰማ፤ ትንሽ አገራዊ ስሜቴ ይኮረኩረኝ ነበር፡፡
ዛሬ ከእነ አቤቤና ሽሜ ዲስኩር ጋር እዚህ አደባባይ ላይ ስሰማው ግን፤ ውስጤ ተረበሸ፣ ቅስሜ ተሰበረ፣ ከምር በአገሬ ተስፋ ቆርጨ አዘንኩ፡፡ ይህ ክተትና ፉከራ፤ እነዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘልቃ ገብታ ወረራ ፈፅማብናለች ስላሏት ጎረቤት አገር ሳይሆን፤ ቅርሷን፣ ባህሏን፣ ታሪኳን ገብራ፣ እራሷን ኢትዮጵያን አምጣና ወልዳ ለተቀረው ህዝብ ላበረከተችው ትግራይ መሆኑን ሳስብ፤ አጥወለወለኝ፡፡
እንደ ሕዝብ ማበዳችን ሲገባኝ ዘገነነኝ! ይህ የእብሪት ሰልፍ ምናልባት ለውጪ ወራሪዎች ቢሆን፤ ከዚህ ተቃራኒ ስሜት ሊሰማኘ ይችል ነበር ብየ አሰብኩ፡፡ ግን በተቃርኖው ሆነና፤ በግድ እናቴን ከቤቴ ውጪልኝ ብዬ፤ ቀጥቅጨ ገፍትሬ የማባረር ያህል፤ ሰቅጣጭ ስሜት ውስጤን ወረረኝ።
“በአንበሳው መኝታ ላይ ጅብ ተኝቶበት፤
ብንን ብንን ይላል በህልሙ እየመጣበት” ብሎ ጓደኛየ ከብስጭትና የተስፋ መቁረጥ ዓለም ቀሰቀሰኝ፡፡
“ምን አልክ?” ስለው፤
"ይቺ አገር ግን ወዴት እየሄደች ነው?" ጥያቄየን በጥያቄ መመለስ አመሉ ነው፡፡
"የት ብለህ ነበር የተሳፈርከው?" የእኔ መልስ አናዶኝ፡፡
"ከምር ወዴት ነው እየሄድን ያለነው? ተገደን የመጣነው ደሞዛችንን እንዳይቆርጡ፤ ከፍ ሲልም ታርጋ እንዳይለጥፉብን እንጂ፤ እነዚህ እኮ ይህንን ሕዝብ አይመጥኑም! ደግሞ አፏን ሞልታ የህልውና አደጋ ትላለች እንዴ? የህልውና አደጋ የገጠማት እራሷ አዳነች አቤቤና ጀሌዎቿ እንጂ፤ ብዙሃኑ ህዝብ ላይ አይደለም! እንኳንስ እዚህ፤ ጁንታው በተቆጣጠረው ላሊበላ ሳይቀር ነዋሪው ተረጋግቶ የእራሱን መስተዳድር አቋቁሞ፤ ሰላሙን አስፍኖ፤ አካባቢውንና ቅርሱን እያስጥበቀ ኑሮውን መምራት ጀምሯል" ጓደኛየን ካልገታኸው፤ እንደክረምት ጅረት ነው የሚወርደው፡፡
"ፊታችንን አስመትተናል፤ በል ይብቃን እንውጣ" ብዬ፤ ለፈረስ ሁለት ሺህ አበል ተከፍሎ፤ እኛ በነፃ ከደነቆርንበት፤ ከዛ ማጎሪያ እንደምንም ብለን በቂ አየር ወደአለበት ቦታ ደረስን፡፡ ዶ/ር ሊያ ግን "በበጎ ፍቃደኝነት" ስም፤ ኮሮናውን ትታ፤ ዶማ ይዛ ቤት ስታፈርስ ነበር የዋለችው አሉ፡፡ ግራ የገባት አገር! ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ማለት ይሄኔ ነው፡፡
አዲስ አበቤው ነኝ፤ የነገ ሰው ይበለን!