የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ - ነሓሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም
Posted: Tue Aug 17, 2021 8:47 am
የአዲስ አበቤው የዛሬ ውሎ
ነሓሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም
የልዩ ሃይል ኮማንደሩ ግድያ ሲገርመን፤ በስላሴ ጓሮ ሊወሽቁት የታየው ጥድፊያ፤ ሚስጥሩ ያልገባንን አኗኗሪዎች፤ በየፊናችን እንድናንሾካሹክ አስገድዶናል! አዲስ አበባ ሕመሟ ከጠናባትና የሹክሹክታ፣ የሃሜት፣ የፍርሃት ከተማ ከሆነች እኮ ጥንት ሊሆናት ነው!
በአዲስ አበባ ሰማይ ስር፤ በመናፈሻ በመዝናኛ በአደባባይ ስም ሲዖል ተገንብቷል፡፡ አባባ ጃንሆይ እንኳን ደም ሲያምራቸው ለቢሾፍቱው ቆሪጥ ያፈሱለትና ይረኩ ነበር አሉ፡፡ የዘንድሮው ንጉስ ግን የትም ሳይሄድ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከዳር እስከ ዳርቻ፤ ደም በደም አድርጎትም አይረካም፡፡
ስለ ኮማንደሩ አብዛኛው ሕዝብ ግን ከድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ ገና በጥዋቱ የአዲስ አበባ ነዋሪንና አኗኗሪን ስልክ ያጨናነቀው ይኸው የሰውየው የአሟሟት ወሬ ነበር፡፡ ሰውየው አኗኗሪ ሳይሆን ዋና ነዋሪ ነበር አሉ! በእነጃዋር ላይ ሲሴር እግር ያዥ አጠንጣኝ ነበር አሉ፡፡ ይቺ "አሉ" "አሉ" የምትል ደዌ እኔንም ሳትጠናወተኝ አልቀረም፡፡
ከመሞቱ ቀደም ብሎ የነበሩ ሰዎች መረጃም ማስረጃም ሹክ ብለዋል አሉ፡፡ አብቹ ጥርስ ውስጥ ሳይሆን መንጋጋ ውስጥ ዘልቆ ነበር አሉ። በአሁኑ ሰዓት እዚህ አገር ግድያ የተለመደ የዕለት ተዕለት ክንውን ከሆነ ሰነባብቷል። በተለይ ጨቅላውን አምኖ ያገለገለና በወገኖቹ ላይ የፈረደ ሁሉ፤ መልሶ አላምጦ ሲውጣቸው ማየቱ የዘወትር አሰልቺ ትዕይንት ሆኗል፡፡ እነዚያን "የትግራይ ብልፅግና" ብለው በሕዝባቸው ዕልቂት ውስጥ እጃቸው በወገናቸው ደም የዋኘውንም አልማራቸውም አሉ፤ ከሁለት ያጣ ብቻም ሳይሆኑ ሁሉንም ያጣ አድርጓቸዋል፡፡
ከቤቴ ወጥቼ ቀጭኗንና ተሳስበሕ ተጠባብቀህ እምታልፍባትን መንገድ እያለፍኩ፤ ለዚያውም አጥር እየተደገፍኩ ከጭቃው ጋር እየተሟገትኩ እየተቆናጠጥኩ እያለሁ፤ "ኮልኮሌው ፖለቲከኛ" ጋር ፊት ለፊት ተገናኘን፡፡ ስለሁሉም ነገር እኔ ላውራ እኔ ልተንትን ስለሚል ነው፤ የሰፈራችን ሰው ኮልኮሌው ፖለቲከኛ ያለዉ፤ እሱም ተቀብሎታል፡፡ በዚያ ላይ ልክ እንደ አብቹ፤ "ልደመጥ፤ እኔን ብቻ ስሙኝ" ሳያንሰው፤ "ልታይ ልታይ" ያበዛል፡፡
ሰላም ተባብለን ሳንጨርስ፤ "እነጌታቸው ረዳ ከመቀሌ ሸሽተው ላሊበላ ገቡ አይደል" ቢለኝ፤ ገረመኝ:: ትንሽነቱ አሳዘነኝ፡፡
"ጌታቸው ሳኒታይዘር ከላሊበላ ደውሎልህ ነበር?" ልለው አስቤ ነበር፡፡ ግን ፈራሁት፤ በልጅነታችን አንድ ሁለት ጊዜ አናድጀው፤ አይሆኑት አድርጎ ጢብ ጢብ ተጫውቶብኛል፡፡ ምላሴን ሰብስቤ ወደ ስራየ ብሄድ ይሻለኛል አልኩና፤ ርእስ የቀየርኩ መስሎኝ፤ "ከ17 ዓመታት ቆይታ በኋላ መሲ ባርሴሎናን መልቀቁን ሰማህ?" አልኩት፡፡
"የምትገርም ሰው ነህ! የመሲ መልቀቅ ከጁንታዎቹ ሽሽት ጋር ምን ያገናኘዋል!" ብሎ ተናዶብኝ ሄደ።
ተመስገን ብየ እየተጣደፍኩ ከማዶ ወደቆመችው የጓደኛዬ መኪና ዘለቅኩ፡፡ ስለ ኮልኮሌው ላስቀው ስል፤ ገና ተመቻችቼ ሳልቀመጥ ወሬውን ቆለለብኝ፡፡ "ይህንን ጉድ ሰምተሃል" አለ፤ ወሬ ስለሚጠማው፤ ወሬው እራሱ እሱን ፈልጎ የሚመጣ ነው የሚመስለው፡፡ የማይጎረገረው ወሬ የለም፡፡
"የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲስተም ሙሉ በሙሉ ዳውን መሆኑን ሰምተሃል? ለዚያውም ዛሬ ስድተኛ ቀኑ ነው" አለኝ በጣም አካብዶ፡፡ ግን እውነቱን ነው በጣም ከባድ ጉዳይ ነው፡፡
"ምን ሆኖ ነው" አልኩት ለተሳትፎ፡፡
"ምንም ሊያውቁት አልቻሉም፡፡ ትኬት ኦፊስ የሚሰራው ጓደኛየ ነው ሹክ ያለኝ፡፡ ብዙ ነገራቸው ተሰናክሎባቸዋል፤ ክፍያ እንኳን አይሰራም፡፡ የውጭ ሃይል እጅ ሳይኖርበት አይቀርም፡፡ እኔ ጁንታውንና አሜሪካንን ነው የምጠረጥረው" ብሎኝ እርፍ፡፡ ወይ እቺ ጁንታ ከዱቄትነት ሃከርም ሆናለቻ! ክፉኛ አሳቀኝ፡፡
ምን ገዶት ጓደኛየ፤ የአየር መንገዱን ሳይቋጨው ወደ ሌላ አርእስት ዘለለ፡፡ ስራ ቦታ ሳንደርስ የቃረመውን ወሬ ሁሉ ካልዘረገፈልኝ፤ ቁርጠት የሚለቅበት ይመስለኛል፤ ለመናገር ይጣደፋል፡፡
"አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ 21 ኦፊስ እንዳላቸው ታውቃለህ" አለኝ፡፡
"እነማን? አየር መንገዶች ናቸው" ስለው፤ እንደመመናጨቅ አለና፤
"አንተ ደግሞ ትቀልዳለህ፤ ኤርትራውያን እንጂ! ከትልቁ ኢምባሲያቸው ሌላ፤ አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ 21 የተሟላ ኦፊሶች አላቸው" ሲለኝ፤ ከምር ለምን እንደሆነ ደነገጥኩኝ ብቻ ሳይሆን ፈራሁኝ፡፡
"ታድያ አንደኛውን ቅኝ ግዛት ሆነናል አትለኝም፡፡ ለመሆኑ ምን የሚያደርጉበት ነው" ከማለቴ ቀጠለ፡፡
"ከተማው ውስጥ ይህ ሁሉ የትግራይ ተወላጅ የሚታደነውና ድርጅቶቹ የሚታሸጉት፤ በእነዚህ በየወረዳው በተከፈቱት የኤርትራውያን ኦፊሶችና፤ በብአዴን የብልፅግና ሰዎች ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆችን ቤት እንዳስፈለጋቸው እየተመላለሱ በመፈተሽ፤ ከገንዘበ ጀምሮ ወርቅ ጌጣጌጥና ያሰኛቸውን ንብረት ነው የሚዘርፉት፡፡ በብር የአገሪቱን ዶላር የሚቸበችቡት በእነዚሁ ኦፊሶች ውስጥ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ኦፊስ ውስጥ በርካታ ኤርትራውያን የደሕንነት ሰራተኞች አላቸው፡፡ የየራሳቸው ቀጠና አበጅተው አዲስ አበባን ተቀራምተዋታል፡፡ በጣም የሚፈልጓቸውን የትግራይ ተወላጆች በዓፋር በኩል ወደ አሰብ ይወስዷቸዋል" ከዚህ በላይ ለመስማት ህሊናየን ቋቅ አለው፡፡
"አንተ የምርህን ነው? ከየት ነው ይህን ለማመን የሚከብድ ጉድ የቃረምከው?" ለነገሩ እሱ የማይደርስበት የወሬ ጉራንጉር የለም፤ ሁሌ የሚያነፈንፈው ደግሞ እውነታውን ነው፡፡
"በሚዲያ ሕግ ምንጭህን ለመናገር የማትገደድ ቢሆንም ላንቺ ነግርሻለሁ፡፡ ያ የኦሆዴዱ ብልፅግና ነው፡፡ ከብአዴን ብልፅግናዎች ጋር በጣም ጥርስ ተናክሰዋል፡፡ ኤርትራውያኑ ደግሞ ከብአዴኖች ጋር ተለጥፈው አዲስ አበባ ባሕርዳር ጎንደር ሁኗል ሃኒ-ሙናቸው፡፡ እናማ የሚያውቀውንና አብረው ሲያቦኩ ሲጋግሩ የነበሩትን ሁሉ አይዘረግፍልኝ መሰለህ፡፡" እያለ ድንገት ፍሬን ያዘ፡፡
ከአንድ የኢምባሲ ግቢ ፊትለፊት ሞቅ ያለ ግርግር አስቆመን፡፡ "ቆይ ቆይ እስቲ" ብሎ መኪናውን ጥግ አስያዘው፡፡ "ምን ሆንክ ሰዓት ደርሶብናል እኮ?" ብለው ሊሰማኝ ነው፤ ዘው ብሎ ወረደ፤ ወሬ አይደል፤ ለወሬ ሟች!
ምን ላድርግ ተከተልኩት፤ "እንዴ! አየህልኝ?" አለ ወደ ትርምሱ መሃል እያመላከተ፡፡ "አንገቱ ላይ ሽርጥ የጠመጠመው ሰውየ ይታይሃል? ይሄ ነገር እኛ ሳንሰማ ሰተት ብለው ገቡ እንዴ?" አለኝ፤ አፉን እንደከፈተ በድንጋጤ፡፡
ባማትር ምንም ሽርጥ አልታይህ አለኝና፤ "እነማን ናቸው የሚገቡት? ከጃፖን የኦሎምፒክ ቡድናችንን ነው?" ስለው፤ "እረ ጁንታዎቹ እንጂ! ፍጥነታቸው እኮ እንደ ሲፈን ሀሰን ሆነብን" አለ፡፡ ለካስ ጁንታው በሰሜን ወሎና በደቡብ ጎንደር ብቻም አይደለም የተንፈላሰሰው፤ ጓደኛየ ልብ ውስጥም ፍርሃትን አስፍኖ፤ ሽርጥና ስካርቭ መለየት ተሳነው፡፡
ግርግሩ ምንድነው ስንል፤ ፖሊሱ ሁሉ ከነቀበሌ ዘበኛው ወደ ጦር ግንባር ዘምቶ፤ መንግስት አልባ እየሆነች ባለችው አዲስ አበባ፤ "የመብራት ሃይል ሰራተኞች፤ የዚህን ሰፈር ትራንስፎርመር ቀይረው፤ ከወዲያ ለሚገኘው ኤምባሲ ሊተክሉ ነው" የሚል ወሬ የሰሙ የዚህ ሰፈር ወጣቶች፤ ፖል እንጨት ላይ ወጥተው ትራንስፎርመር ሲጠግኑ የነበሩትን የመብራት ሃይል ሰራተኞች፤ እመሬት አጋድመው፤ "በሎም" እየተባባሉ ነበር፡፡
ጓደኛየ በማያገባው ሁሉ አይደል የሚገባው፤ ወደ አንዱ ጠጋ ብሎ፤ "አረ ገላግሏቸው፤ እንደዚህ እኮ ሕጋዊ አይደለም" ሲለው፤... ብልጭ አለበትና፤ ጮክ ብሎ፤ "ምነው ጀለስ፤ አንተም የመብራት ሃይል ሰራተኛ ነህ እንዴ?" ብሎ ኮሌታውን፡፡ ምን ይዋጠኝ፡፡ ሁሌ የምፈራውና የምሸሸው ጠብ ዱላ፤ በደረስኩበት ሁሉ እንደተከተለኝ ነው፡፡
ከዚያማ፤ ጓደኛየንም አንድ ሁለቴ "በሎም" ሲሉት፤ "ፈሪ ለናቱ! እምየ ድረሽልኝ!" ብየ እግሬ ወደ መራኝ ሽሽት፡፡ ከዚያማ የምን ውሎ የምን ስራ! ማታ እቤት ስገባ አባየ ስለሽሽት ሲያወራ ደረስኩ፡፡ ምን ሰምቶብኝ ነው ብየ ሳዳምጥ፤ ወሬው ሌላ ነው፡፡ ወሎ መርሳ ከተማ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ጦር፤ ተራራው ሁሉ ጁንታ መስሎ ታየውና፤ ገና ጥይት ሳይተኮስ፤ ከመርሳ የሸሸ ውርጌሳንና ውጫሌን አቋርጦ፤ ሓይቅ ሳይደርስ አይቀርም መባሉን፤ ከዘመዶቹ ጋር ተደዋውሎ የቃረመውን ነው የሚያወራው፡፡ እድሜ ለብልፅግና፤ በወሬ ነግቶ በወሬ ይመሻል!
ነገን ማየትም ለብዙዎች ብርቅ እየሆነ ነውና፤ የለማንኛውም የነገ ሰው ይበለን! አዲስ አበቤው ነኝ!