በዚህ ሳሚንት ብቻ ከ3 ሺህ በላይ የቅማንት ብሔር አባላት ጦርነት ሽሽት ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ሱዳን ድንበር መሻገራቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።
ብላታ ጎሹ የተባሉ ስደተኛ በበኩሉ "አማራዎች ከትግራይ ጋር እያካሄዱ ባሉት ጦርነት እየደገፋችሁን አይደላችሁም በማለት እኛን እየወጉን ነው" ብለዋል። "ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ሰዎች በቆንጨራ ታርደዋል፣ አስክሬኖችን አንስተን መቅበር እንኳን አልቻልንም፣ በመንግሥት የሚደገፉ የአማራ ተዋጊዎች ከመሬታችን ተነቅለን እንድንሄድ ይፈልጋሉ። እየገደሉን ያሉት የብሔራችን ቁጥር አነስተኛ ስለሆነ ነው" በማለት የተናገረችው ደግሞ የ20 ዓመቷ እመቤት ደሞዝ ናት።
ለዓመታት ውጥረት እየተባባሰ ነበር የምለው ከጎንደር ከተማ የተፈናቀለው የ26 ዓመቱ አማን ፈረደ፤ መጀመሪያ አካባቢ ግጭቱ በእኛና በአማራ ብሔር መካከል ነበር፤ አሁን ግን ግጭቱ መልኩን ቀይሮ እየወጋን ያለው መንግስት ነው ይላል። እንደ ካሳው አባይ እምነት ደግም "አማራ የትግራዩን ግጭት ወደ ሌሎች መሬት ለመስፋፋት እንደ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀመበት ይገኛል።"
"እነሱ ሁሉንም መሬት የራሳቸው አድርገው ያስቡታል። ስለዚህ እኛንም ሆነ ትግራዮችን ማየት አይፈልጉም" ያሉት ደግሞ አንድ የ50 ዓመት ተፈናቃይ ናቸው።
በዘገባው እንደተመላከተው ቅማንቶች ለዘመናት በአማራ የባህልና ኢኮኖሚ ተጽዕኖ ስር ከቆዩ በኋላ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የምስልና የዜና ምንጫችን AFP ነው።
የቅማንት ብሔረሰብ አባላት በአማራ ክልል እየተፈጸመባቸው ባለው ጥቃት ሽሽት ወደ ሱዳን እየተሰደዱ እንደሚገኙ ታወቀ
-
- Posts: 404
- Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm