እውነት ከሆነም ታላቅ ክብር፤ ካልሆነም ያልታሰበ ሲሳይ ነው!

Post Reply
africangear
Posts: 404
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

እውነት ከሆነም ታላቅ ክብር፤ ካልሆነም ያልታሰበ ሲሳይ ነው!

Post by africangear »

የህወሓት ነባርም ሆኑ የወቅቱ መሪዎች የሞቱት በስድሳዎቹ ወደ በርሃ የወረዱ ጊዜ ነው። በዕድል ተርፈው ለመንግስትነት ከበቁ በኋላ የኖሩትን ኖሮ ትርፍ ሂወት ነው። በዕድል በተረፈችው ሂወትም ቢሆን ግን ከነጎደሎው ብዙ ለኣገሪቱ የጠቀሙ ቁምነገሮች ሰርተውበታል። ከዓለም ማህብረሰብም ኣድኖቆት ኣግኝተውበታል። እነዚህ ሂወታቸው ሙሉ ለኢትዮጵያ ብዙ የከፈሉ የዘመኑ ጀግኖች ኣራት ኪሎና ኣስመራ ቤተመንግስት በሰፈሩ የቂም ሃይሎች ሲከዱም ዕድሜ፣ ጤና እና የንሮ ሁኔታ ሳይገድባቸው የህዝባቸውን መስዋእት የተከፈለበት መብት ኣሳልፈው ላለመስጠት ሲሉ በክብር መስዋእት መሆን የመረጡ የጀግኖች ሁሉ ጀግኖች ናቸው።

ስለሆነም እስከ ኣሁን የተባለው የደመሰስናቸው ገድልናቸው ዜና እውነት ከሆነም መስእዋትነቱ በታላቅ ክብር ተቀብለን እነሱ ያስተማሩት ዛሬ በየትኛውም የፖለቲካ ጎራ የሚገኝ በሚሊዮን የሚቆጠር የኣዲሱ ትውልድ ኣባል እና ዛሬ በትግራይ በራሃዎችና ተራሮች ኣስደናቂ ገድል እየፈጸመ ያለው ጀግናው የትግራይ መከላከያ ሃይላችን በጋራ በመሆን የተሰበረውን ለመጠገን፣ የጎደለውን ለመሙላት እና ካሁን በፊት ያልተገኘውን ጭምር ለማግኘት ሁሉ ትግሉን ያቀጣጥላል። እየተባለ ያለው እውነት ካልሆነም ደግሞ እነዚህ ትርፍ ሂወት እየኖሩ ያሉት የዘመኑ ጀግኖች የኣዲሱን ትውልድ ድል ለማየት ስለሚበቁ እሰየው ሳይታሰብ የተገኘ ሲሳይ ነው ብለን ኣጋጣማዊን ኣድንቀን እና ኣመስግነን እናልፈዋለን።

ከዚህ በዘለለ በስድሳዎቹ ለመስዋእት የወሰኑና በኣጋጣሚ የተረፉ ሂወቶች መኖርና ያለመኖር ጉዳይ ኣያስጨንቀንም። ኣይገባምም። ይልቁንስ ከዛሬው የትግል ኣጀንዳው ኣንዲት ኢንች ማፈግፈግ አንደማይፈልግ በየቀኑ እያስመሰከረ ያለውን እያንዳንዱ ትግራዋይ ይህ የጨካኞች ግፍና መከራ እየወረደበት ያለውን ህዝብና ክልል ነፃ እስኪወጣ ድረስ ያባቶቹን ጀግንነት በተሻለና ዘላቂ በሆነ ድል እንዲቋጭ ይታገላል።

ትግሉ ከጨካኞች፣ ስግብግቦች እና ከኋላ ቀሮች ጋር በመሆኑ ኣሁንም ተጨማሪ ዋጋ ያስከፍለናል። ነገር ግን ድሉ የተገፋው ህዝብ እንደሚሆን ሳትጠራጠሩ በሚመጣው ትውልድ እየተወሳ የሚኖር የራሳችን ኣሻራ እንድናኖር ትግሉን የመቀላቀል ዕድሉ ዛሬ ብእጃችን ነው።

ኣገር ነበርን ኣገር እንሆናለን።

ገብረ ሥላሴ ኣርኣያ


Post Reply