ከ ሙርከኛው የአማራ ልዩ ሃይል ኣንደበት

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 404
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

ከ ሙርከኛው የአማራ ልዩ ሃይል ኣንደበት

Post by africangear »

Amhara-special-force-POW.jpg
ታጋይ ጌታቸው ኣረጋዊ ከ ሙርከኛው የአማራ ልዩ ሃይል ጋር

መልሰው ዋሴ ዋለ ይባላል። ተወልዶ ያደገው ባህርዳር ከተማ ነው። በ 1991 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት ወታደር ሁኖ ተቀላቀለ። እስከ 2004 ዓ/ም አገልግሎ የ አምሳ አለቃ መዓርግ ደርሶ በ ፍላጎቱ ተሰናብቶ በሲቪል ስራ በተለያዩ መስርያቤቶች ስያገለግል ቆየ። ኣሁን ሐምሌ 20, 3013 በባህርዳር ከተማ የክፍለ ከተማ ገቢዎች ሰራትኛ ሁኖ ሲሰራበት ከነበረ ተጠርቶ "የአማራ /ኢትዮጵያ የህልውና ዘመቻ" ክተት ኣዋጅ ታውጆ ተገድዶ ዘመቻው እንደተቀላቀለ ነው የሚናገረው። "እጄ ላይ ጉዳት ስለ ነበረኝ ይተውኛል ስል 'ኣይ ኣይሆኑም፡ አማራ ሊጠፋ ነው አድን' ብለው ኣስገቡኝ" ይላል። "በተግባር ግን አገር እና ህዝብ እያጠፋ ያለው አሁን ያለው የብልፅግና አመራር እንጂ፡ የማረከኝ ሃይል (የትግራይ ሰራዊት) እማ እኔ የተዋጋሁትን ሰው ጨምሮ ህዝቡ እየተንከባከበ ነው ያለው" ይላል መልሰው።

ሓምሌ 24, 2013 ዓም በ ሰ/ወሎ ዞን ግዳን ወረዳ ከሙጃ ከተማ ወጣ ብሎ ከወልድያ ወደ ባህርዳር በመወስደው መንገድ ነው የተማረከው። ከወልድያ ወደ ባህርዳር በመወስድ ዋና መንገድ ኣንጎት በሚባል ወረዳ ፡ ቀበሮ ሜዳ በምትባል ትንሽ ከተማ በኛ ሓይሎች እንክብካቤ እና ምክር ተስጦት ነው እግዝሄሩን እያመሰገነ በሰላም ተረጋግቶ አርፎ ያለው ምርኮኛው የአማራ ልዩ ሃይል መልሰው ዋሴ።

ተጋዳላይ ጌታቸው ኣረጋዊ (ውራይና)


Post Reply