የጋይንት ሕዝብ ከ31 ዓመት በፊት ከትግራይ ታጋዮች ጋር የነበረውን የትግል አጋርነት ታሪክ ደገመ

Ethiopia related news and publications
Post Reply
africangear
Posts: 404
Joined: Fri Dec 11, 2020 5:07 pm

የጋይንት ሕዝብ ከ31 ዓመት በፊት ከትግራይ ታጋዮች ጋር የነበረውን የትግል አጋርነት ታሪክ ደገመ

Post by africangear »

TDF-with-amhara-people-in-Guna.jpg

የጋይንት ሕዝብ ከ31 ዓመት በፊት ከትግራይ ታጋዮች ጋር የነበረውን የትግል አጋርነት ታሪክ እየደገመ ነው!

"...እናንተማ የጥንቶቹ የእኛዎቹም አይደላችሁ! ስለሕዝብ በጀግንነት መሰዋት እንጂ፤ የሰው ሃብትና ሴት የማትነኩት፤ የ1980ዎቹም አይደላችሁ! ... ታዲያ ምን ያደርጋል፤ እንዲያ አብረን ከታገልን ከተሰዋን በሁዋላ፤ ኢህድን ለሚባል አውሬ ጥላችሁን ሄዳችሁ እንጂ!..." የጋይንት ወላጆች ለትግራይ ሰራዊት የሚያሰሙት ተደጋጋሚ ሕዝባዊ ድምፅ ነው::

የጋይንት ሕዝብ እንደ 1980ቹ ሰሞኑን በተለይም ዛሬ፤ ከትግራይ ሰራዊት ጎን ተሰልፎ፤ በሁሉም መስክ ዓቅሙ የፈቀደውን ሁሉ እያደረገ፤ ሰራዊቱን በመንከባከብ ላይ ይገኛል::

ከዓመታት በፊት ኢሕድን(ብአዴን) የምስረታ በዓሉን ሲያከብር፤ አብዛኞቹን የኢሕአዴግ ድሎች የብቻው ገድል አስመስሎ፤ በተቆጣጠረው ሚዲያ ሲያቀርብ ሲያናፋ ያስተዋሉ የጋይንት ወላጆች፤ ግርም ብሏቸው እያለ፤ እነሳሞራ በዚያ ሲያገድሙ አስቆሟቸውና፤ "...ምነው እኛ በህይወት እያለን! ባለታሪኮቹ ጀግኖቹ በህይወት እያላችሁ? ምነው ጉና ደብረታቦርን ያልዋሉበትን እኛ ነበርን ጀግኖቹ እንዲሉ ፈቀዳችሁላቸው!?" ማለታቸው አገሩ በሚዲያ የሰማው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር!

እኒያ የጥዋቶቹ የትግራይና የጋይንት ጀግኖች ዳግም ተገናኝተው፤ ዛሬም ጉና ላይ ታሪክ እየተሰራ ነው:: እህል ለመቅመስ አረፍ ያለ አንድ የትግራይ ሰራዊት አዛዥ፤ አንድ የጋይንት እናት ያሉትን በስሜት ሲያጫውተኝ፤

“...የዚህ አካባቢ ሕዝብ ድሮ ሆነ ዘንድሮም፤ የሚበላ ይሁን የሚቀመስ ሲያቀርብልህ፤ እራሱ ሳይቀምስ አይሰጥህም! መተማመንን ለማጠንከር ነው:: እና እኝህ እናት የሚጠጣ ቀምሰው እየሰጡኝ፤ ስሜን ጠሩና፤ '...እንደው በሞቴ፤ ዘንድሮም ለሌላ አሳልፋችሁ ጥላችሁን ትሄዱ ይሆን?...' አሉኝ:: ገፅታቸው ላይ ስጋት ይነበባል:: ከ31 ዓመት በፊትም ወጣት ታጋይ ሆኜ እዚሁ ግንባር ተሳትፌ ስለነበር፤ ይህንን ሕዝብ በደንብ አውቀዋለሁ:: ጠንካራ ታታሪ ሰራተኛ፣ ጀግና ሃይማኖተኛ እውነትን አፍቃሪ፣ ላመነበት የሚሰዋ ሕዝብ ነው" አለኝ::


Post Reply